ፊደላት
የግእዝ ቋንቋ እንደ ሌሎች ቋንቋዎች እራሱን የቻለ ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ የሚነገር ጥንታዊ ቋንቋ ነው፡፡ አንድን ቋንቋ እንደ ቋንቋ ከሚያስቆጥሩት መሠረታዊ ነገሮች አንዱ እና ዋንኛው የራሱ የሆኑ ፊደላት ሲኖሩት እና የራሱን የአነጋገር ሥርዓት ተከትሎ መሄድ ሲችል ነው፡፡ ይህም በመሆኑ በዛሬ አምዳችን ስለ ግእዝ ቋንቋ ፊደላት ብዛትና የፊደላቱንም ስያሜ ትርጒም እንመለከታለን፡፡
- የግእዝ ፊደላት አጠቃላይ ብዛት ፳፮ (26) ነው፡፡
- የግእዝ ፊደላት በሰባት የአዘራዘር ስልት ይዘረዘራሉ፡፡
- የግእዝ ፊደላት ብዛት ከነ አዘራዘራቸው ፻፹፪ (182) ናቸው፡፡
ይህም ማለት እየአንዳንዱ ፊደል በሰባት ሥልት ስለሚዘረዘር ነው፡፡
ምሳሌ: ሀ. ግእዝ ሁ. ካዕብ ሂ. ሣልስ ሃ. ራብዕ ሄ.ሐምስ ህ.ሣድስ ሆ. ሣብእ ከፊደል ሀ እስከ ፐ ያሉት ፊደላት በዚህ ዓይነት መንገድ ይዘረዘራሉ፡፡
በፊደል ገበታ ላይ የምናገኛቸው የፊደላት ብዛት አጠቃላይ ፴፫ (33) ሲሆኑ ቀሪዎቹ ፯ (ሰባት) ፊደላት የአማርኛ ፊደላት በመባል ይጠራሉ፡፡ እነዚህን ፊደላት ከነ አዘራዘራቸው በሌላ ጊዜ እናያቸዋለን፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ፳፮ (26)ቱን የግእዝ ፊደላት በቅደም ተከተል ከነትርጒማቸው እንመለከታለን፡፡